- የሌሊት ሶላት መቆምን መተው እንደሚጠላና ይህም በሸይጧን አማካይነት እንደሚሆን ተረድተናል።
- በርሱና አላህን በመታዘዝ መካከል እንቅፋት ለመሆን በሁሉም መንገድ ላይ የሰውን ልጅ ለመከልከል ከሚቀመጠው ሸይጧን መጠንቀቅ እንደሚገባ ተረድተናል።
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: (ወደ ሶላት ያልቆመ) በሚለው የተፈለገው ማንኛውም የሶላት አይነትም ሊሆን ይችላል፤ ተለይቶ የታወቀን ሶላት ሊሆንም ይችላል፤ የለይል ሶላትም ሊሆን ይችላል፤ የግዴታ ሶላትም ሊሆን ይችላል።
- ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: «ቦታው ላይ ለመጥቀስ ከእንቅልፍ ጋር አብሮ የሚሄደው አካል አይን ከመሆኑም ጋር ጆሮን ለይተው የጠቀሱት የእንቅልፉን ክብደት ለመግለፅ ነው። መስሚያዎች መንቂያ አካላቶች ናቸውና። ሽንት የተለየበት ምክንያትም ደሞ ወደ ውስጥ ለመግባት ቀላልና ወደ ደም ስር ለመስረፅ ፈጣን ስለሆነ ነው። ይህም ከሆነ በኋላ ለሁሉም አካል መስነፍን ያወርሳል።»