- ሶላት ውስጥ መመሰጥና ልብን መጣድ አንገብጋቢ መሆኑን እንረዳለን። ሰይጣንም ሶላት ውስጥ በመወስወስና በመጎትጎት ይታገላል።
- ሰይጣን ሶላት ውስጥ በሚወሰውስ ወቅት ወደ ግራ ከመትፋት ጋር ሶስት ጊዜ "አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧኒ አርረጂም" ሶስት ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - በሚያጋጥማቸው ችግሮች ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ችግራቸውን እስኪፈቱላቸው ድረስ ወደርሳቸው እንደሚመለሱ መገለፁን እንረዳለን።
- የሶሐቦች ልብ ህያው መሆኑን እንረዳለን። ሀሳባቸው ሁሉ መጪው አለም ነው።