ከቡረይደህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል...
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞችና በሌሎች ከሀዲያንና መናፍቃን መካከል ያለው መተማመኛና ቃል ኪዳን ሶላት እንደሆነና ሶላትን የተወ ሰውም በርግጥ እንደካደ ገለፁ።

ከቡረይደህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: 'በኛና በነርሱ (በከሀዲዎች) መካከል ያለው (መለያ) ቃል ኪዳን ሶላት ነው። ሶላትን የተወ ሰው በርግጥም ክዷል።'"

ከጃቢር (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦ 'በሰውየውና በሺርክ፣ በክህደት መካከል ያለው (ግርዶ) ሶላትን መተው ነው።'"

ከሳሊም ቢን አቢ ጀዕድ እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: "አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: 'ምናለ ሰግጄ እረፍት ባገኘሁ።' አለ። ሰዎቹ በዚህ ንግግሩ ላይ ያነወሩት መስሎ ሲታይም እንዲህ አለ: 'የአላህን መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: ‹ቢላል ሆይ! ሶላትን ኢቃም ብለህ በሶላት እረፍት ስጠን።›'"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለሶላት ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ ከመቅራታቸው በፊት ትንሽ ዝም ይሉ ነበር። እኔም የአላህ መልክተኛ ሆይ! እናትና አባቴ ፊዳ ይሁንሎና በተክቢራ እና በፋቲሓ መካከል ዝምታዎን አይቻለሁና ምንድን ነው የሚሉት? አልኳቸው። እርሳቸውም " 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመጝሪብ አልላሁምመ ነቂኒ ሚን ኸጧያየ ከማ ዩነቃ አሥሠውቡል አብየዹ ሚነድደነስ፣ አልላሁምመ ኢጝሲልኒ ሚን ኸጧያየ ቢሥሠልጂ ወልማኢ ወልበረድ' ነው የምለው" አሉኝ። (ትርጉሙም: አላህ ሆይ! በምስራቅና በምዕራብ መካከል እንዳራራቅከው በኔና በወንጀሌ መካከል አራርቅ! አላህ ሆይ! ነጭ ልብስ ከእድፉ እንደሚጠራው እኔንም ከወንጀሎቼ አጥራኝ! አላህ ሆይ በጤዛ፣ በውሃና በበረዶ ከወንጀሎቼ እጠበኝ። ማለት ነው።)»

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና ለሩኩዕ ተክቢራ በሚያደርጉ ጊዜ እጃቸውን በትከሻቸው ትይዩ ከፍ ያደርጉ ነበር። ልክ እንደዚሁ ከሩኩዕ ራሳቸውን ቀና ያደረጉ ጊዜም እጃቸውን ከፍ ያደርጉ ነበር። "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ፣ ረበና ወለከል ሐምድ" ይሉም ነበር። ሱጁድ ላይ ግን ይህንን አያደርጉም ነበር።»

ከዑባዳህ ቢን ሷሚት (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም።"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) መስጂድ ገቡ። አንድ ሰውዬም መስጂድ ገባና ሰገደ። ነቢዩንም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም ሰላምታውን መለሱና እንዲህ አሉት "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" ቀደም ብሎ እንደሰገደው ለመስገድ ተመለሰ። ቀጥሎም በመምጣት ለነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሰላምታ አቀረበላቸው። እርሳቸውም "ተመለስና ደግመህ ስገድ! አንተ አልሰገድክም።" እያሉት ሶስት ጊዜ ተመላለሰ። እርሱም "ያ በእውነት በላኮት ጌታ እምላለሁ! ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" አላቸው። እርሳቸውም "ወደ ሶላት የቆምክ ጊዜ ተክቢራ አድርግ፤ ከዚያም ከቁርአን (ፋቲሓንና) የገራልህን ቅራ! ከዚያም በተረጋጋ ሁኔታ አጎንብስ፤ ከዚያም ቀጥብለህ በቆምክበት እስክትረጋጋ ድረስ ተነሳ፤ ከዚያም በሱጁድህ እስክትረጋጋ ድረስ ሱጁድ አድርግ፤ ከዚያም ተረጋግተህ እስክትቀመጥ ድረስ ተነሳ! በሁሉም የሶላትህ ክፍልም ይህንን ፈፅም።" አሉት።»

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: አቡ ሁረይራ ግዴታ ሶላቶችም ሆኑ ሱና ሶላቶች በረመዳን ውስጥም ሆነ በሌላ ወቅት በሁሉም ሶላቶች ሲሰግድ ተክቢራ ያደርግ ነበር። በሚቆም ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ሩኩዕ በሚያደርግ ጊዜ ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም "ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" "አላህ ላመሰገነው ሰው ሰሚ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ሱጁድ ከመውረዱ በፊትም "ረበና ወለከል ሐምድ" "ጌታችን ላንተ ምስጋና የተገባ ነው።" ይላል፤ ከዚያም ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም "አሏሁ አክበር" ይላል፤ ከዚያም ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ወደ ሱጁድ በሚወርድ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም መልሶ ራሱን ከሱጁድ በሚያነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል፤ ከዚያም ከሁለተኛው ረከዐ መቀመጥ በኃላ በሚነሳ ጊዜም ተክቢራ ያደርጋል። ሶላቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ በየሁሉም ረከዐ ይህንን ይፈፅማል። ከዚያም በጨረሰ ጊዜ እንዲህ ይላል: " ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ እኔ ከአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት ጋር ለመመሳሰል እጅግ የቀረበውን ሶላት የምሰግድ ነኝ። ዱንያን እስኪለያዩ ድረስ ይህቺው ነበረች አሰጋገዳቸው።"

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "በሰባት አጥንቶቼ ሱጁድ እንዳደርግ ታዝዣለሁ። በግንባሬ በማለት በእጃቸው ወደ አፍንጫቸው አመላከቱ፣ በሁለቱ እጆቼ፣ በሁለቱ ጉልበቴ፣ በሁለቱ እግር ጣቶቼ ፤ ልብሳችንንም ይሁን (ለወንዶች) ፀጉራችንን እንዳንሰበስብም ታዘናል።"

ከአቡ ኡማማ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዐምር ቢን ዐበሳህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ እንደሰማቸው ነገረኝ: "ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው በመጨረሻው የሌሊቱ አጋማሽ ነው። በዚህ ወቅት አላህን ከሚያወሱ መሆን ከቻልክ ሁን!"»

ጀሪር ቢን ዐብደላህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ ነበርን። የ14ኛዋን ሌሊት ጨረቃ ተመለከቱና እንዲህ አሉ: ' ይህን ጨረቃ እንደምትመለከቱት ጌታችሁንም በርግጥ ታያላችሁ። እርሱን ለማየትም ምንም አትቸገሩም። ፀሀይ ከመውጣቷና ከመግባቷ በፊት ባለው ሶላት ላይ አለመሸነፍን ከቻላቹ አድርጉት።' ቀጥሎ ይህንን አንቀፅ አነበቡ: '{ጌታህንም ከማመስገን ጋር ፀሀይ ከመውጣቷ በፊት ከመግባቷም በፊት አወድሰው።}'"

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በፈጅር ሁለት ረከዓዎች ላይ {ቁል ያ አዩሃል ካፊሩን} እና {ቁል ሁወሏሁ አሐድ}ን አነበቡ።"