- ሶላቱ ጮክ ተብሎ የሚቀራበት ቢሆን እንኳ ዱዓንና የሶላት መክፈቻን ዝግ አድርጎ ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
- ሶሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በእንቅስቃሴም ይሁን እርጋታ ላይ ያላቸውን ሁኔታ በማወቅ ላይ ያላቸውን ጥረት እንረዳለን።
- ሌሎችም የመክፈቻ ዱዓዎች መጥተዋል። በላጩ ሰውዬው ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የመጡትንና የፀኑትን የመክፈቻ ዱዓዎች በመከተልና በመሸምደድ አንዳንዴ ይሄንን አንዳንዴ ደግሞ ሌሎቹን እየቀያየረ ቢል ነው።