- አንድ ሙስሊም በሌሊቱ የመጨረሻ ወቅት ላይ ዚክር እንዲያደርግ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- በተለያዩ ወቅቶች ዚክር ለማለት፣ ዱዓ ለማድረግና ለመስገድ አንዱ አምልኮ ከአንዱ እንደሚበላለጥ እንረዳለን።
- "ጌታ ወደ ባሪያው እጅግ ቅርብ የሚሆነው" በሚለው ሐዲሥና "አንድ ባሪያ ወደ ጌታው እጅግ ቅርብ የሚሆነው ሱጁድ ላይ ሆኖ ነው።" በሚለው ሐዲሥ መካከል ባለው ልዩነት ሚረክ እንዲህ ብለዋል: እዛኛው ላይ የተፈለገው ጌታ ወደ ባሪያ እጅግ ቅርብ የሚሆነው የሌሊቱ አጋማሽ ላይ ሲሆን እዚህኛው ላይ የተፈለገው ደግሞ አንድ ባሪያ ካሉት ሁኔታዎች መካከል ወደ ጌታ የሚቀርበው በሱጁድ ሁኔታው መሆኑን ለመግለፅ ነው።