- ሶላት ላይ በሰባት አካላት ሱጁድ ማድረግ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- ልብስንና ፀጉርን ሶላት ውስጥ መሰብሰብና መጠቅለል እንደሚጠላ እንረዳለን።
- አንድ ሰጋጅ ሶላት ውስጥ የመረጋጋት ግዴታ አለበት። ይህም ሰባቱን የሱጁድ አካላት መሬት ላይ በማሳረፍና የተደነገገውን ውዳሴ እስኪፈፅም ድረስ እዛው ላይ በመርጋት ነው።
- ፀጉርን የመጠቅለል ክልከላው በወንዶች ላይ ብቻ የተገደበ ነው። ሴት ልጅ ሶላት ውስጥ እንድትሸፋፈን (እንድትሰተር) የታዘዘች ናትና።