- እነዚህ የሶላት ማዕዘኖች ናቸው። በመርሳትም ይሁን ባለማወቅ መተው አይቻልም። የዚህም ማስረጃው ነቢዩ ሰጋጁን ማስደገማቸው ነው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እርሱን በማስተማር ብቻ አልተብቃቁም። ይልቁንም እንዲደግመው አዘዙት።
- ሶላት ውስጥ መረጋጋት ከሶላት ማእዘናት መካከል አንዱ ነው።
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ከሶላት ግዴታዎች መካከል አንዱን ያጓደለ ሶላቱ እንደማይበቃ ያስረዳናል።"
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ለተማሪና አላዋቂ ሰው ማዘንና ለስላሳ መሆን እንደሚገባ፤ ጉዳዩን ለርሱ ግልፅ ማድረግና የተፈለገበትን አላማ ብቻ ማሳጠር እንደሚገባ፤ በርሱ ደረጃ ያሉ ሰዎች ሊሸመድደውና ሊተገብረው የማይችላቸውን ግን-ደግሞ ማሟያ የሆኑ ዕውቀቶችን ትቶ ወሳኝ የሆኑ ነገሮችን ብቻ በማስተማር መቆጠብ እንደሚገባም ያስረዳናል።"
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ሙፍቲ አንድ ነገር ሲጠየቅ ጠያቂው ከጠየቀው ውጪ ሊነገረው የሚያስፈልገው ሌላ ነገር ካለ ባይጠይቀው እንኳ ለርሱ መዘርዘር እንደሚወደድ ያስረዳናል። ይህም የማይጠቅምን ከመናገር መካከል የሚመደብ ሳይሆን ከመመካከር የሚመደብ ነው።"
- "ከዚህ ውጪ አሳምሬ መስገድ አልችልምና አስተምሩኝ።" ከሚለው ንግግር ጉድለትን ማመን ያለውን ደረጃ እንረዳለን።
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ያለውን ደረጃ፤ ተማሪ ዐሊም እንዲያስተምረው መጠየቅ እንደሚገባው እንረዳለን።"
- በመገናኘት ወቅት ሰላምታ መለዋወጥ እንደሚወደድ፤ ሰላምታ መመለስ ግዴታ መሆኑን፤ በአጭር ወቅት እንኳ ቢሆን በተደጋጋሚ ከተገናኙ ሰላምታን መደጋገሙ እንደሚወደድና ሁሉንም የሚቀርቡለት ሰላምታዎች መመለስ ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን።