- ሶላት ውስጥ እጆችን ከፍ ከማድረግ ጥበቦች መካከል: የሶላት ውበት መሆኑና አላህን ማላቂያ መሆኑ ተጠቃሽ ነው።
- ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅ ከፍ የሚደረግበት አራተኛ ስፍራ መጥቷል። እሱም ከአቡ ሑመይድ አስሳዒዲይ እንደተወራውና አቡዳውድና ሌሎቹም በዘገቡት ሐዲሥ ባለሶስትና ባለአራት ረከዓ ሶላቶች ላይ የመጀመሪያውን ተሸሁድ ብለው (ለሶስተኛው ረከዓ) በሚቆምበት ወቅት ነው።
- በተጨማሪ ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጃቸውን በጆሯቸው ትይዩ ጆሯቸውን ሳይነኩ ከፍ ያደርጉ እንደነበር መጥቷል። ይህም ማሊክ ቢን ሑወይሪሥ ባስተላለፉትና ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተክቢራ ያደረጉ ጊዜ እጃቸውን በጆሯዋቸው ትይዩ እስኪሆን ድረስ ከፍ ያደርጉት ነበር።"
- " ሰሚዐሏሁ ሊመን ሐሚደህ" እና "ረበና ለከል ሐምድ" አንድ ላይ የሚለው ኢማምና ብቻውን የሚሰግድ ሰው ብቻ ናቸው። ተከታይ የሆነ ሰው ግን "ረበና ወለከል ሐምድ" ብቻ ነው የሚለው።
- ከሩኩዕ በኋላ "ረበና ወለከል ሐምድ" ማለት ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአራት የቃላት ይዘት የመጣ ሲሆን ይህቺም አንዷ ናት። በላጩ ግን አራቱንም የቃላት ይዘት ("ረበና ወለከል ሐምድ" ፤ "አልላሁምመ ረበና ወለከል ሐምድ" ፤ "ረበና ለከል ሐምድ" ፤ "አልላሁምመ ረበና ለከል ሐምድ") በመከታተልና በመሸምደድ አንዳንዴ በዚህ አንዳንዴ በዛ እያቀያየሩ ማለቱ ነው።