- ከወንጀሎች መካከል ከባባድና ትናንሽ የሚባሉ እንዳሉ፤
- ትናንሽ ወንጀሎች የሚሰረዙት ከባባዶቹን ወንጀሎች መራቅን እንደመስፈርት ማሟላት ከተቻለ መሆኑን እንረዳለን።
- ከባባድ ወንጀሎች የሚባሉት ወይ በዱኒያ ቅጣት የተወሰነባቸው፣ ወይም በአኼራ የሚያስከትሉትን የቅጣት አይነት የተነገረባቸው፣ ወይም የአላህ ቁጣ የመጣባቸው፣ ወይም ከባድ ዛቻ ያለባቸው፣ ወይም ደግሞ አድራጊው የተረገመባቸው ሲሆኑ ነው። ለምሳሌ፡ ዝሙት፣ መጠጥ መጠጣት ይጠቀሳሉ።