- የሶላትና የባሪያዎች መብት ጉዳይ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመከሯቸው ምክሮች የመጨረሻዎቹ ምክር መሆናቸው የሶላትና የባሪያዎች መብት ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ያስረዳናል።
- ሶላት አላህ በባሮቹ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል ትልቁ ሐቅ ነው። የፍጡራንን ሐቅ መወጣት በተለይ የደካሞችና ከልጆቻችን ውጪም ቢሆኑ በእጆቻችን ስር የምናስተዳድራቸውን ሰዎች ሐቅ መጠበቅ ከትላልቅ የፍጡራን ሐቆች መካከል አንዱ ነው።