- የባሪያውን ወንጀል የሚያስምረው ሶላት ዉዱኡን ያሳመረበትና የአላህን ፊት በመፈለግ በተመስጦ የሰገደው ሶላት ነው።
- በአምልኮ ላይ የመዘውተር ትሩፋትን እንረዳለን። አምልኮ ትናንሽ ወንጀሎችን የሚያስምር አንዱ ሰበብ ነው።
- ዉዱእን የማሳመር፣ ሶላትን የማሳመርና በሶላት ውስጥ የመመሰጥን ትሩፋት እንረዳለን።
- ትናንሽ ወንጀሎች እንዲማሩ ትላልቅ ወንጀሎችን መራቅ ወሳኝ እንደሆነ እንረዳለን።
- ትላልቅ ወንጀሎች በተውበት ካልሆነ በቀር አይማሩም።