- የፋቲሐን ታላቅነት እንረዳለን። የላቀው አላህ "ሶላት" ብሎ ጠርቷታል።
- ባሪያው አላህን በማመስገኑ፣ በማወደሱና በማላቁ ብቻ አላህም ባሪያውን ማወደሱ የጠየቀውንም እንደሚሰጠው ቃል መግባቱ አላህ ለባሪያው የሰጠውን ትኩረት ግልፅ ያደርግልናል።
- ይህቺ የተከበረች ምእራፍ አላህን ማመስገንን፣ የመመለሻውን ዓለም ማስታውስን፣ አላህን መለመንን፣ አምልኮን ለአላህ ማጥራትን፣ ወደ ቀጥተኛው መንገድ መመራትን መጠየቅን፣ ከጥመት መንገዶች ማስጠንቀቅን ሰብስባለች።
- አንድ ሰጋጅ ፋቲሐን በሚቀራ ጊዜ ይህንኑ ሐዲሥ ማስተዋሉ ሶላቱ ውስጥ የሚኖረውን ተመስጦ ይጨምርለታል።