/ በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ።

በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ።

ከዐብደላህ ቢን መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ "ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ጠየቅኳቸው። እሳቸውም 'ሶላትን በወቅቱ መስገድ።' አሉ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'ቀጥሎ ለወላጆች መልካም መዋል ነው።' አሉኝ። 'ከዚያስ ቀጥሎ' አልኳቸው። እርሳቸውም 'በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ። እነዚህን ነገሩኝ። ጥያቄዬን ብጨምር እርሳቸውም ይጨምሩልኝ ነበር።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጁ ስራ ምን እንደሆነ ተጠየቁ። እርሳቸውም "ግዴታ ሶላቶችን አላህ በገደበው ወቅት መስገድ ነው።" ብለው መለሱ። ቀጥሎም በጎ በማድረግ፣ ሐቃቸውን በመጠበቅ፣ ሐቃቸውን ከመጨፍለቅ በመቆጠብ ለወላጆች መልካም መዋል ነው። ቀጥሎም የአላህን ንግግር የበላይ ለማድረግ፣ ከኢስላምና ከተከታዮቹ ጠላቶችን ለመመከትና የኢስላምን ምልክቶች ይፋ ለማድረግ በአላህ መንገድ መታገል ነው። ይህም በነፍስና በገንዘብ ነው። ኢብኑ መስዑድ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እነዚህን ስራዎች ነገሩኝ። ለርሳቸው 'ከዚያስ ቀጥሎ' ብላቸው ኖሮ ግን ይጨምሩልኝ ነበር።" አሉ።

Hadeeth benefits

  1. ስራዎች በመካከላቸው የሚበላለጡት አላህ ለስራዎቹ ባለው ውዴታ ልክ ነው።
  2. ሙስሊምን እጅግ በላጭ በሆነ ስራ ላይ እንዲጓጓ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ በላጭ ስራዎች ተጠይቀው የሚመልሱት መልስ እንደጠያቂዎቹ ሰዎችና ሁኔታቸው መለያየት ይበላለጣል። እያንዳንዱን ጠያቂ ለነርሱ እጅግ በጣም ጠቃሚ የሆነውን መልስ ነው የሚመልሱት።