- ሴት ልጅ የወር አበባ ቀናቷ በሚጠናቀቅበት ወቅት መታጠብ ግዴታዋ መሆኑን እንረዳለን።
- የበሽታ ደም በሚፈሳት ላይም ሶላት ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- የወር አበባ ማለት: ተፈጥሯዊ ደም ሲሆን የደረሰች ሴት ማህፀን በብልት በኩል የሚለቀው ደም ነው። የሚከሰትባትም በታወቁ ቀናት ውስጥ ነው።
- የበሽታ ደም ማለት: ያለ ወቅቱ ከማህፀን ጥልቁ ክፍል ሳይሆን ከማህፀን አቅራቢያ ክፍል የሚፈስ ደም ነው።
- በወር አበባና በበሽታ ደም መካከል ያለው ልዩነት: የወር አበባ ደም ጥቁር፣ ወፍራምና ሽታው የሚከረፋ ነው። የበሽታ ደም ግን ቀይ፣ ቀጭንና የሚከረፋ ሽታም የሌለው ነው።