- ከሌሊት እንቅልፍ በኋላ የመፋቅ ድንጋጌ አፅንዖት የተሰጠው መሆኑን እንረዳለን። ይህም እንቅልፍ የአፍ ጠረን እንዲለወጥ አንዱ ምክንያት ስለሆነ ነው። መፋቂያም የማፅጃ አንዱ መሳሪያ ነው።
- የአፍ ጠረን ወደ መጥፎ ጠረን በሚለወጥበት ወቅት ባጠቃላይ መፋቅ አፅንዖት ተሰጥቶት የተደነገገ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። ይህም ቀደም ተብሎ የተጠቀሰውን ሀሳብ በመያዝ ነው።
- ጥቅል በሆነ መልኩ ማፅዳት የተደነገገ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን። ንፅህና ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሱናና ከምርጥ ስነ ምግባር አንዱ ነው።
- አፍን ባጠቃላይ መፋቅ ሲባል ጥርሶችን፣ ድድንና ምላስንም ያካትታል።
- መፋቂያ ማለት "አራክ" ከሚባል ዛፍ ወይም ከሌላ የዛፍ አይነት የሚቆረጥ እንጨት ነው። አፍንና ጥርስን ለማፅዳትም ያገለግላል። አፍን ያፀዳል፣ መጥፎ ጠረንንም ያስወግዳል።