- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በኡመታቸው ላይ ያላቸው እዝነትና እንዳይከብድባቸውም የሚጠነቀቁላቸው መሆናቸውን እንረዳለን።
- የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ትእዛዝ ሱና መሆኑን የሚጠቁም ማስረጃ እስካልመጣ ድረስ በመሰረቱ ግዴታ ነው።
- ሁሉም ሶላት ዘንድ የመፋቅን ተወዳጅነትና ያለውን ትሩፋት እንረዳለን።
- ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዲህ ብለዋል: «ወደ ሶላት በሚቆም ወቅት መፋቅ የተወደደበት ጥበብ ሶላት ወደ አላህ መቃረቢያ ወቅት ስለሆነ ነው። ይህ ደሞ አምልኮውን ማላቅህን ለማንፀባረቅ ሲባል የተሟላ ሁኔታንና ንፁህ መሆንን ይጠይቃል።»
- የሐዲሡ ጥቅል ሀሳብ ፆመኛ እንኳን ቢሆን ፀሃይ ዘንበል ካለች በኋላም መፋቁ እንደሚወደድለት ያካትታል። (ፆመኛ ሁኖ) በዙህርና ዐስር ሶላት ወቅት መፋቅን ይመስል።