- ትጥበት ሁለት አይነት ነው። እነሱም: ከግዴታ የሚያብቃቃ ትጥበትና የተሟላ ትጥበት ናቸው። ከግዴታ የሚያብቃቃው ትጥበት: ሰውዬው ጦሀራ ማድረግን ነይቶ ከመጉመጥመጥና አፍንጫ ውስጥ ውሃን ከመክተት ጋር ሰውነቱን በውሃ ማዳረሱ ነው። የተሟላው ትጥበት ደግሞ: በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደታጠቡት መታጠብ ነው።
- ጀናባ የሚለው ቃል የዘር ፈሳሽ ያፈሰሰን ወይም የዘር ፈሳሽ ባያፈስ እንኳ ግንኙነት የፈፀመን ሁሉ የምትገልፅ ቃል ናት።
- ባለ ትዳሮች የሆኑ አንዱ የሌላኛውን ሀፍረተ ገላ መመልከትና ከአንድ እቃ ውሃ እየወሰዱ መታጠብ እንደሚፈቀድላቸው እንረዳለን።