- የውሻ ምራቅ ከባድ ነጃሳ ነው።
- ውሻ እቃ ውስጥ ምላሱን በመንከር መጠጣቱ እቃውንም ውስጡ ያለውን ውሃም ይነጅሰዋል።
- በአፈር ማፅዳትና በውሃም ሰባት ጊዜ መደጋገም የውሻ ሽንት፣ ሰገራና ሌሎችም ውሻ ያቆሸሻቸው ነገሮች የሚፀዱበት አፀዳድ ሳይሆን በአፉ የነካ ጊዜ ብቻ የሚፈፀም የአፀዳድ አይነት ነው።
- እቃ በአፈር የሚፀዳበት የአፀዳድ አፈፃፀም: እቃ ውስጥ ውሃ ያደርግና አፈር ይጨምርበታል። ቀጥሎ በዚህ ከአፈር ጋር በተቀላቀለ ውሃ የተነጀሰውን እቃ ያጥባል።
- የሐዲሡ ግልፅ መልዕክት ሸሪዓ ቤታችን እንድናደርጋቸው የፈቀዳቸውን ውሻዎችንም ሳይቀር የአደን፣ የጥበቃ፣ ለአዝርእትና ከብቶች ጥበቃ የምናሳድጋቸውን ውሻዎች ይመስል ሁሉንም ውሻዎች ያጠቃልላል።
- ሳሙናና እንዶድ የአፈርን ቦታ አይተኩም። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለይተው አፈር ብለው በግልፅ ስላስቀመጡ ነው።