- አይነ አፋርነቱ በሰው አማካኝነት እንኳ ከማስጠየቅ አለማቀቡ የዐሊይ ቢን አቢጧሊብን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል።
- ፈትዋ ለመጠየቅ ሰው መተካት እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- አንድ ሰው ስለራሱ የሚያሳፍር ነገርንም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ መናገሩ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- የመዚይን ነጃሳነትና ከሰውነትም ከልብስም ላይ ማጠብ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- የመዚይ መውጣት ዉዱእን ከሚያፈርሱ ነገሮች መካከል አንዱ መሆኑን እንረዳለን።
- ብልትንና ሁለቱን ፍሬዎች ማጠብ እንደሚገባ የሚያዝ ሌላ ሐዲሥ ስላለ ብልትንና ሁለቱን ፍሬዎች ማጠብም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።