- ከእንቅልፉ ለነቃ ሰው ሁሉ ከአፍንጫው የሸይጧንን ፋና ለማስወገድ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ ማውጣት እንደተደነገገ እንረዳለን። ዉዹእ የሚያደርግ ከሆነ ደግሞ በዚህ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሃ እየከተተ በማውጣት መታዘዙ ይበልጥ አፅንዖት የተሰጠው ጉዳይ ይሆናል።
- ከአፍንጫ ውሃ ማስወጣቱ አሟልቶ ወደ አፍንጫ ውሃ ከማስገባት የሚመደብ ነው። ወደ አፍንጫ ውስጥ ውሃ ማስገባት የአፍንጫን ውስጥ ማፅዳት ነው። ማስወጣቱ ደግሞ ከውሃው ጋር ቆሻሻውን እንዲወጣ ማድረግ ነውና።
- ሐዲሡ ውስጥ "ያድራልና" የሚለው ቃል ይህ ድርጊት በምሽት እንቅልፍ መገደቡን ያስረዳናል። ማደር ከምሽት እንቅልፍ ውጪ አይሆንምና። ይህም የምሽት እንቅልፍ መርዘምና ጥልቅ እንቅልፍ የሚጠረጠርበት ቦታ ስለሆነ ነው።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ሸይጧን የሰው ልጅ በማያውቀው መልኩ ከርሱ ጋር አብሮ እንደሚቆራኝ ይጠቁማል።