- የባህር እንስሳ ቢሞት ሐላል ነው። ውስጡ የሞተ በማለት የሚፈለገው: በባህር ውስጥ ካልሆነ በቀር የማይኖር ሆኖ እዛው ውስጥ የሞተን ነው።
- የተሟላ ጥቅም እንዲገኝ ጠያቂ ከጠየቀው በበለጠ መመለስ እንደሚገባ እንረዳለን።
- ውሃ ውስጡ በገባበት ንፁህ ነገር ጣዕሙ ወይም ቀለሙ ወይም ሽታው ቢለወጥ ውሃው በተፈጥሮ ባህሪው ላይ እስከቀረ ድረስ ጨዋማነቱ ወይም ትኩስነቱ ወይም ቀዝቃዛነቱና የመሳሰሉ ነገሮች ቢበረቱ ራሱ አፅጂ እንደሆነ ይቀራል።
- የባህር ውሃ ትንሹንም ሆነ ትልቁን ሐደሥ ያነሳል። ንፁህ በሆነ ሰውነት ወይም ልብስ ወይም ከዛ ውጪ ላይ ያረፈን ነጃሳ ራሱ ያስወግዳል።