/ የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል።...

የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል።...

ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡- “አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ፡- " የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ (ከእርሶ መላክ በፊት ባለው የድንቁርና ዘመን) በሠራነው ሥራ እንቀጣለን?" ነቢዩም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉት፡- "በኢስላም ሥራውን ያሳመረ፥ በጃሂሊያ በሠራው ሥራ ተጠያቂ አይሆንም። እስልምናን ተቀብሎም መጥፎ የሠራ ግን በቀድሞውም በኋለኛውም ስራው ይጠየቅበታል። "
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት አብራሩ። እስልምናውን አሳምሮ፣ እውነተኛና ሙኽሊስ (ያጠራ) ሆኖ የሰለመ ሰው ከመስለሙ በፊት በሠራው ወንጀል አይጠየቅም። ወደ እስልምና ከገባ በኋላ ሙናፊቅ በመሆን ወይም ከእምነቱ በመውጣት መጥፎ የሠራ ግን በክህደት ዘመኑም ሆነ በእስልምና ዘመኑ ስለ ሠራው ሥራ ይጠየቃል።

Hadeeth benefits

  1. ሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና በጃሂሊያ ዘመን ለሰሩት ስራ የሰጡት ትኩረትና ፍርሃታቹውን እንረዳለን።
  2. በእስልምና ላይ መፅናት መበረታታቱ፤
  3. ወደ እስልምና የመግባትን ትሩፋት እንረዳለን። እሱም ያለፈውን መጥፎ ስራዎች ማስማሩ ነው።
  4. ከእስልምና የወጣና ሙናፊቅ የሆነ ሰው ቀደም ብሎ ከመስለሙ በፊት ስለ ሠራቸው ሁሉ ሥራዎችና በእስልምና ውስጥም ስለ ሰራቸው ሁሉ ወንጀሎች ይጠየቃል።