/ ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።

ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።

ሐኪም ቢን ሒዛም -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጃሂሊያ ዘመን በምፅዋት፣ ነፃ በማውጣትና ዝምድና በመቀጠል የምፈፅማቸው አምልኮዎች ነበሩ በእነሱ እመነዳለውን?" አልኳቸው። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለው መለሱለት፦ "ካሳለፍከው መልካም ተግባር ጋር ነው የሰለምከው።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ካፊር የሰለመ ጊዜ ከመስለሙ በፊት በጃሂሊያ ዘመን ይሠራቸው በነበሩት እንደ ሰደቃ፣ ባሪያን ነፃ ማውጣትና ዝምድና መቀጠል የመሰሉ መልካም ሥራዎች እንደሚመነዳ አብራሩ።

Hadeeth benefits

  1. ካፊር በዱንያ ለሠራቸው መልካም ሥራዎች በዛው ክህደት ላይ ከሞተ በአኺራ አይመነዳበትም።