- የአላህ እዝነትና ምህረት ሰፊ መሆኑንና ደረጃውንም እንረዳለን።
- የተውሒድን ትሩፋት እንረዳለን። አላህ ለተውሒድ ሰዎች ወንጀልና ሀጢዐታቸውን ይምራል።
- የሺርክን አደጋና አላህ አጋርያንን እንደማይምርም እንረዳለን።
- ኢብኑ ረጀብ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ወንጀልን የሚያስምሩትን ሶስት ሰበቦች አጠቃልሏል። የመጀመሪያው: ከመከጀል ጋር ዱዓ ማድረግ ነው። ሁለተኛ: ምህረትን መጠየቅና ንስሀን መፈለግ ነው። ሶስተኛ: በተውሒድ ላይ መሞት ነው።»
- ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጌታቸው ከሚያወሩት ሐዲሥ መካከል አንዱ ነው። "ሐዲሠል ቁድሲይ" ወይም "ሐዲሠል ኢላሂይ" በመባልም ይጠራል። ይህም ማለት ቃሉም መልዕክቱም ከአላህ የሆነና ነገር ግን በማንበቡ እንደማምለክ፣ ለርሱ ዉዱእ ማድረግና የርሱን አምሳያ አምጡ ብሎ አላህ መገዳደሩን የመሰሉ የቁርአን መለዮዎች የሌለው ነው።
- ወንጀሎች ሶስት አይነቶች ናቸው: የመጀመሪያው: በአላህ ማጋራት ነው። ይህም አላህ የማይምረው ወንጀል ነው። አላህ ዐዘ ወጀል እንዲህ ብሏል {እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ።} ሁለተኛው: አንድ ባሪያ በርሱና በጌታው መካከል ባለው ጉዳይ በወንጀልና ሀጢዐት ነፍሱን መበደሉ ነው። ይህንንም አላህ ከሻ የሚያልፈውና ይቅር የሚለው ነው። ሶስተኛ: አላህ አንዳችም የማይተወው ወንጀል ነው። እርሱም: ባሮች አንዳቸው አንዳቸውን መበደላቸው ነው። ይህንንም የግድ የማመሳሰል ፍርድ ተፈፃሚ ይሆንበታል።