- የተውበት በር ክፍት እስከሆነ ድረስ ተቀባይነቷም ይቀጥላል። ፀሀይ ከመግቢያዋ በመውጣቷ ደግሞ በሩ ይዘጋል። ልክ እንደዚሁ ጣእረ ሞት - ማለትም ነፍስ ልትወጣ ጉሮሮ ጋር - ከመድረሱ በፊት ንስሀ መግባትም ይገባዋል።
- በወንጀል ተስፋ መቁረጥ እንደማይገባ፤ የአላህ ይቅር ባይነትና እዝነት ሰፊ መሆኑን እንዲሁም የተውበት በርም ክፍት መሆኑን እንረዳለን።
- የተውበት (ንስሀ) መስፈርቶች: የመጀመሪያው: ከወንጀሉ መውጣት ነው። ሁለተኛው: ወንጀሉን በመፈፀሙ መፀፀት ነው። ሶስተኛው: ወደ ወንጀሉ ዳግመኛ ላይመለስ መቁረጥ ነው። እነዚህ መስፈርቶች ግን የተጣሰው የአላህ መብቶች ብቻ ከሆነ ነው። ከፍጡራን ሐቆች ጋር የተያያዘ ወንጀል ከሆነ ግን ንስሀው ትክክለኛ እንዲሆን ይህን ሀቅ ወደ ባለቤቱ መመለስ ወይም ከባለቤቱ ይቅርታን ማግኘት ተጨማሪ መስፈርት ነው።