- አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ስፋቱን ፤ የሰው ልጅ ምንም ያክል ወንጀል ቢሰራ ወደ አላህ ተውበት ካደረገና ከተመለሰ አላህ ተውበቱን እንደሚቀበለው፤
- በአላህ ያመነ የጌታውን ይቅርታ ተስፋ ያደርጋል፣ ቁጣውንም ይፈራል፣ ወደ ተውበት ይቻኮላል እንጂ በወንጀል ላይ አይቀጥልም።
- የትክክለኛ ተውበት መስፈርቶች: ከወንጀል መውጣት፣ በወንጀሉም መፀፀት፣ ዳግም ወደ ወንጀል ላለመመለስ መቁረጥ ነው። ተውበት የሚያደርገው ባሮችን በገንዘብ ወይ በክብር ወይ በነፍስ ከመበደል ወንጀል ከሆነ አራተኛ መስፈርት ይጨመራል። እሱም: ተበዳዩ ባለመብት ሀላል እንዲያደርግለት (ዓውፍ እንዲለው) መጠየቅ ወይም ሓቁን መስጠት ነው።
- አንድን ባሪያ ስለዲኑ ጉዳይ አዋቂ የሚያደርገው የሆነውን አላህን ማወቅ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ተረድተናል። ስለአላህ ማወቁ ወንጀል በሰራ ቁጥር ተስፋ ሳይቆርጥና ወንጀሉ ላይ ሳይዘልቅ እንዲቶብት ያደርገዋልና።