- አስተዋይ የሆነ ሰው ወደ ተውበት መቻኮል ይገባዋል። በበደል ላይ የዘወተረ ጊዜ አላህ አዘናግቶ እንደሚይዘው መጠራጠር የለበትም።
- አላህ በዳዮችን ማዘግየቱና እነሱን በመቅጣት አለመቻኮሉ እነሱን ማዘናጊያና ካልቶበቱ ቅጣታቸውን ማነባበርያ ነው።
- ግፍ የአላህን ቅጣት ህዝቦች ላይ የሚያመጣ አንዱ ምክንያት ነው።
- አላህ አንድን መንደር ሲያጠፋ በውስጧ ደጋጎችም ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህ ደጋጎች የትንሳኤ ቀን በሞቱበት መልካምነት ላይ ሆነው ነው የሚቀሰቀሱት። ምድራዊ ቅጣቱ እነሱንም ማካተቱ በመጪው አለም አይጎዳቸውም።