- መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዐሊይን አላህና መልክተኛው እንደሚወዱት እርሱም አላህና መልክተኛውን እንደሚወድ መመስከራቸው የዐሊይን ቢን አቢ ጧሊብ (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ደረጃ ያስረዳናል።
- ሶሐቦች ለመልካም ነገር ያላቸውን ጉጉትና እሽቅድድም እንረዳለን።
- በውጊያ ወቅትም ቢሆን ስነ-ስርዓት እንደተደነገገና አላስፈላጊ የሆኑ አስደንጋጭ ድምጾችና መራወጥ መተው እንደሚገባ እንረዳለን።
- የርሳቸውን ነቢይነትን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል በየሁዶች ላይ ድል እንደሚያደርጉ ተናግረው መከሰቱና በአላህ ፈቃድ በርሳቸው እጅ የዐሊ ቢን አቢጧሊብ አይኖች መፈወሱ ነው።
- ከጂሃድ የሚፈለገው ትልቁ አላማ ሰዎች ወደ እስልምና እንዲገቡ ማድረግ ነው።
- ዳዕዋ (ጥሪ) ቀስ በቀስ ነው የሚከወነው። ከከሀዲ መጀመሪያ የሚፈለገው ሁለቱን የምስክርነት ቃላቶችን ተናግሮ ወደ እስልምና እንዲገባ ነው። ቀጥሎ ከዚህ በኋላ የእስልምና ግዴታዎችን ይታዘዛል።
- ወደ እስልምናና እስልምና ውስጥ ወዳሉ መልካሞች በመጣራት የሚገኘው ትሩፋት ለተጣሪውም ለተጠሪውም ነው። ተጠሪው ቅኑን ጎዳና ያገኛል፤ ተጣሪው ደግሞ ትልቅ ምንዳ ይመነዳል።