- ከቁርኣን አንቀፆች ግልፅ የሚባሉት መልእክቱ ፍንትው ያለና ትርጉሙ ግልፅ የሆነ ነው። አሻሚ የሚባሉት ደግሞ ከአንድ በላይ በርካታ ትርጓሜ ያዘለ እንዲሁም ለመረዳት ጥናትና ግንዛቤ ያስፈለገው አንቀፅ ነው።
- የጥመትና የቢድዐ ባለቤቶችን፣ ሰዎችን ለማሳሳትና ጥርጣሬ ውስጥ ለመክተት አወናባጅ ነጥቦችን የሚጥል ሰውን ከመቀላቀል መጠንቀቅ፤
- የአንቀፁ መጨረሻ ክፍል ላይ {የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} በሚለው የአላህ ንግግር ውስጥ ጠማሞችን መቃወምና በእውቀት የጠለቁትን ማሞገስ አለ። ማለትም፦ ያልተገሰፀና ያልተመከረ ስሜቱንም የተከተለ ከአእምሮ ባለቤቶች አይደለም ማለቱ ነው።
- አሻሚ አንቀጾችን መከታተል ለልቦና ጥመት መንስኤ ነው።
- ትርጉማቸው የማይገባ የሆኑ አሻሚ አንቀጾችን ወደ ግልፅ አንቀጾች መመለስ ግዴታ መሆኑን፤
- አላህ ሰዎችን ለመፈተንና የኢማን ባለቤቶች ከጥመት ባለቤቶች እንዲለዩ የቁርኣንን ከፊል ግልፅ ከፊሉን ደግሞ አሻሚ አድርጓል።
- ቁርኣን ውስጥ አሻሚ አንቀጾች መካተታቸው ዑለሞች ከሌላው አንፃር ያላቸውን ደረጃ የሚገልፅና አይምሮ አቅሟ የተገደበ መሆኑን አውቃ ለፈጣሪዋ እጅ መስጠትና ድክመቷን ማወቅ እንዳለባት እንረዳለን።
- በዕውቀት መጥለቅ ያለው ደረጃና በዕውቀት መፅናት አስፈላጊነቱን እንረዳለን።
- {(ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁትም} በሚለው አንቀፅ ላይ "አላህ" የሚለው ላይ ሲደርስ በመቆም ዙሪያ የተፍሲር ልሂቃን ዘንድ ሁለት አቋም አለ። "አላህ" የሚለው ጋር ሲደርስ የቆመ "ፍቺውን" በማለት የሚፈለገው:- ለማወቅ የማይቻል የሆኑ የአንድን ነገር ትክክለኛ ምንነትን ፍቺ አላህ እንጂ አያውቀውም። ለምሳሌ ስለነፍስ፣ ስለቂያማ ዕለትና ሌሎችም አላህ በዕውቀቱ የተነጠለበት ጉዳዮች። በእውቀት የጠለቁት ግን በሱ ያምናሉም ይቀበላሉም በዚህም ምክንያት ይድናሉ።
- "አላህ" የሚለው ጋር ሲደርስ ያልቆመ "ፍቺውን" በማለት የተፈለገው "ትርጓሜውን" ማለት ይሆናል። ትርጓሜውን አላህና በእውቀት የጠለቁት ያውቁታል። ያምኑበታልም ወደ ግልፅ የቁርኣን አንቀፅም ይመልሱታል ማለት ይሆናል።