- ሐዲሡ የርሳቸውን ነቢይነት ከሚጠቁሙ ሐዲሶች መካከል አንዱ ነው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በኡመታቸው ውስጥ የሚከሰተውን መናገራቸውና እንደተናገሩት ከመከሰቱ አንፃር ነው።
- ነፍሱን ዝግጁ እንዲያደርግና ባጋጠመው ወቅት ታጋሽና ምንዳውን የሚያስብ ሊሆን ዘንድ ለተፈተነ ሰው ለወደፊት ያጋጥመዋል ተብሎ የሚታሰብ መከራን ማሳወቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- ከቁርአንና ሐዲሥ ጋር ያለ ትስስርን ማጠንከር ከፈተናና ልዩነት መውጫ መንገድ እንደሆነ እንረዳለን።
- ለመሪዎች በመልካም ጉዳይ መስማትና መታዘዝ ላይና ግፍ እንኳ ቢያደርሱ በነርሱ ላይ አምፆ ባለመውጣት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- በፈተና ዘመን ሱናን መከተልና ጥበብን መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።
- አንድ ሰው በርሱ ላይ ግፍ እንኳ ቢደርስበት ባለበት እውነት ላይ መቆም እንደሚገባው እንረዳለን።
- ይህ ሐዲሥ አንድ መርህን ይጠቁመናል። እርሱም፦ ከሁለት ክፋቶች ዝቅተኛውን ክፋት ይመረጣል፤ ወይም ከሁለት ጉዳቶች ቀላሉ ጉዳት ይመረጣል የሚል ነው።