- ወደ መልካም ነገር መጠቆም መበረታታቱን ፤
- መልካም በመፈፀም ላይ መቀስቀስ የሙስሊሙ ማህበረሰብ እርስ በርስ እንዲተባበሩና እንዲዋሃዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ መሆኑን ፤
- የአላህ ችሮታ ሰፊ መሆኑን ፤
- ሀዲሱ ሁሉን የሚያካትት መርህ ስለሆነ በውስጡ ሁሉም መልካም ስራዎች የሚገቡ መሆኑን ፤
- የሰው ልጅ የጠያቂን ፍላጎት ማሳካት ካልተመቻቸለት ለጠያቂው የሚያሳካለትን ሌላ አካል መጠቆም እንዳለበት እንረዳለን።