- ይህ ሐዲሥ መጥፎ ነገርን የማስወገድ እርከኖችን በማብራራት ረገድ መሰረት ነው ።
- መጥፎን ነገር ደረጃ በደረጃ መከልከል እንደሚገባና፤ ሁሉም በችሎታውና በአቅሙ ልክ መከልከል እንደሚገባው መታዘዙ።
- መጥፎን ነገር መከልከል ከማንም ላይ የማይወርድ ሀላፊነትና ሁሉም ሙስሊም በችሎታው ልክ እንዲሰራው የሚገደድበት የእስልምና ትልቅ ህግ (የዲን ምዕራፍ) ነው።
- በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ከኢማን ክፍሎች መካከል አንዱ መሆኑ፤ እንዲሁም ኢማን የሚጨምርና የሚቀንስ መሆኑ።
- ከመጥፎ ለመከልከል የሚከለክሉት ድርጊት መጥፎ መሆኑን ማወቅ መስፈርት ነው።
- መጥፎን ነገር ለመለወጥ ከተቀመጡ መስፈርቶች መካከል ፦ ከሚለውጠው መጥፎ ነገር የባሰ መጥፎ ውጤት አለማስከተሉ አንዱ ነው።
- እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቃቸው የሚገቡ ከመጥፎ ለመከልከል የተቀመጡ ስርአቶችና መስፈርቶች አሉ።
- መጥፎን ማውገዝ ሸሪዓዊ ብልሀት ፣ ዕውቀት እና እርግጠኝነት (ማስረጃ) ይፈልጋል።
- በቀልብ አለማውገዝ የኢማን ድክመትን ይጠቁማል።