- ማህበረሰቡን ለመጠበቅና ለማዳን በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል አንገብጋቢ መሆኑን እንረዳለን።
- ሀሳቡ ህዋሳዊ (በተጨባጭ ምስል ከሳች) በሆነ መልኩ ለአእምሮ ቀለል እንዲል ምሳሌዎችን መጠቀም ከማስተማር መንገዶች መካከል አንዱ ነው።
- ግልፅ የሆነ ውግዝ ተግባር ያለምንም አውጋዥ መፈፀሙ ጉዳቱ ወደ ሁሉም የሚመለስ ብክለት ነው።
- የማህበረሰብ ውድመት መጥፎ ሰዎች በምድር ላይ ብልሽትን ሲያሰራጩ ችላ ማለትን ተከትሎ የሚመጣ መዘዝ ነው።
- የተሳሳተ እርምጃ በጥሩ ኒያም ቢሆን ስራን አያስተካክልም።
- በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ ያለ ተጠያቂነት የጋራ ነው እንጂ በግለሰብ ላይ ብቻ የሚወሰን አይደለም።
- የውስን ሰዎች ወንጀል ካልተወገዘ ህዝቡን የሚጠቀልል ቅጣት እንደሚያስከስት እንረዳለን።
- ልክ እንደሙናፊቆቹ የክፉ ስራ ባለቤቶችም መጥፎ ስራቸውን ለማህበረሰቡ ግልፅ የሚያደርጉት መልካም ስራ አስመስለው ነው።