- በትንሹም ሆነ በብዛት ወደ ቅናቻ መጣራት ያለውን ደረጃ እንረዳለን። ተጣሪ ሰው በርሱ ጥሪ የሰሩ ሰዎችን ምንዳ አምሳያ ይኖረዋል። ይህም የአላህን ትልቅ ችሮታና ሙሉ ቸርነት ያስረዳናል።
- በትንሹም ሆነ በብዛት ወደ ጥመት የመጣራትን አደጋ እንረዳለን። ወደ ጥመት የሚጣራም ሰው በሰበካው የሰራን ሰው ወንጀል አምሳያ በርሱ ላይ ይኖርበታል።
- ምንዳ የሚሰጠው በስራው አይነት እንደሆነ እንረዳለን። ወደ መልካም የተጣራ ሰው በጥሪው የሰራን ሰው ምንዳ አምሳያ ለርሱ ይኖረዋል። ወደ መጥፎ የሰበከ ሰውም በሰበካው የሰራን ሰው ወንጀል አምሳያ በርሱ ላይ ይኖርበታል።
- አንድ ሙስሊም ወንጀልን ግልፅ በማድረጉ ሰዎች አይተው እንዳይከተሉት መጠንቀቅ አለበት። በዚህ ላይ ሆን ብሎ ባይቀሰቅስ እንኳ በተከተሉት ሰዎች ልክ ወንጀል ላይ ይወድቃልና።