- ለወደፊት የሚከሰቱ ሩቅ ነገሮችን መናገራቸውና እንደተናገሩት መከሰቱ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነቢይነት ከሚጠቁሙ ነገሮች መካከል አንዱ ነው።
- ውግዝ ተግባርን መውደድና በርሱ ላይ መተባበር አይፈቀድም። ውግዝን ማውገዝም ግዴታ ነው።
- መሪዎች ከሸሪዓ የተፃረረን ነገር የፈጠሩ ጊዜ በዚህ ላይ እነርሱን መታዘዝ አይፈቀድም።
- በሙስሊም መሪዎች ላይ አምፆ መውጣት ያልተፈቀደው ይህን ተከትሎ ብክለት፣ ደም መፋሰስና የደህንነት ቀውስ ስለሚከሰት ነው። የወንጀለኛ መሪዎችን ውግዝ ተግባር መቻልና አስቸጋሪነታቸውን መታገስ ከነዚህ ነገሮች አንፃር እጅግ ቀላል ነው።
- ሶላት ጉዳዩዋ (ደረጃዋ) ትልቅ ነው። ሶላት በክህደትና ኢስላም መካከል የምትለይ መሆኗን እንረዳለን።