- ዘካ የመስጠት ግዴታነትንና ዘካ የከለከለ ሰውም ብርቱ ዛቻ እንደተዛተበት እንረዳለን።
- ዘካን በስንፍና የሚከለክል ሰው ከሃዲ ባይሆንም ነገር ግን ከባድ አደጋ ውስጥ እንደሆነ እንረዳለን።
- የሰው ልጅ አምልኮ ሲተገብር የአምልኮውን መሰረት አስቦ ዝርዝሩን ባያስብም በሚከሰቱ ዝርዝር ነገሮች ሁሉ እንደሚመነዳ እንረዳለን።
- በገንዘብ ላይ ከዘካ ውጪም ሐቆች እንዳሉ እንረዳለን።
- ከግመል ሐቆች መካከል አንዱ የምትጠጣበት ስፍራ ባለችበት ወቅት ለሚገኙ ሚስኪኖች አልቦ ማጠጣት ነው። ይህም ፈላጊዎች ቤት ድረስ አስበው ከመምጥት ይልቅ ቀላል ስለሆነና ለግመሎቹም ምቹ ስለሆነ ነው። ኢብኑ በጧል እንዲህ ብለዋል: ገንዘብ ሁለት ሐቆች አሉት: የነፍስ ወከፍ ሐቅና ሌላ ሐቅ ነው። አልቦ ማጠጣት የመልካም ስነምግባር መገለጫ ከሆኑ ሐቆች መካከል አንዱ ነው።
- ከግመል፣ ከከብትና ከፍየል ግዴታ ሐቆች መካከል ኮርማዋን የፈለገች ጊዜ ኮርማዋን ማዘጋጀት ነው።
- የአህያና ማስረጃ ያልመጣባቸው ነገሮች ባጠቃላይ ብይን: {የብናኝ ክብደት ያክልም መልካም የሰራ ሰው ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሰራ ሰው ያገኘዋል።} በሚለው የአላህ ንግግር ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።
- በአንቀፁ ውስጥ መልካም ስራ ትንሽ እንኳ ብትሆን በመስራት ማነሳሳትና መጥፎ ስራ ብታንስ እንኳ ከመስራት ማስጠንቀቂያ አለበት።