- ኹጥባ በሚደመጥበት ወቅት መጥፎን ማውገዝ ወይም ሰላምታን መመለስና ያስነጠሰን "የርሐሙከላህ" ማለትን እንኳ ቢሆን ማንኛውም ንግግር መናገር ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
- ኢማሙን የሚያወራ ወይም ኢማሙ የሚያወራው ሰው እዚህ ክልከላ ውስጥ አይካተትም።
- አስፈላጊ ከሆነ በሁለቱ ኹጥባዎች መካከል ማውራት ይፈቀዳል።
- ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተወሱ ድምፅህን ቀንሰህ በሳቸው ላይ ሶላትና ሰላም ታወርዳለህ። ልክ እንደዚሁ ዱዓ ሲደረግም በዝግታ (ድምፅህን ቀንሰህ) አሚን ትላለህ።