- በአዛንና ኢቃም መካከል ሶላት መስገድ ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።
- ንግግርን መደጋገም የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መመሪያ እንደሆነ እንረዳለን። ይህም የሚናገሩት ነገር አንገብጋቢ መሆኑን አፅንዖት ለመስጠትና ለማሰማት ብለው ነው።
- በሁለት አዛን በማለት የተፈለገው: አዛንና ኢቃምን ነው። (ሁለቱ አዛኖች) ያሉት ወደ አንዱ በማመዘን ነው። (ፀሃይና ጨረቀን) ሁለቱ ጨረቃዎች እንደሚባሉት፣ (አቡበከርና ዑመር) ሁለቱ ዑመሮች እንደሚባሉት ማለት ነው።
- አዛን ማለት ወቅት መግባቱን ማሳወቂያ ነው። ኢቃማህ ማለት ደግሞ ሶላት መፈፀሚያ ወቅቱ መድረሱን ማሳወቂያ ነው።