- አምልኮ የተመሰረተው በቁርአንና ሐዲሥ ላይ በመጣው ላይ ስለሆነ አላህን የምናመልከው በደነገገው ድንጋጌ መሰረት እንጂ በተፈጠሩና በተፈበረኩ አምልኮዎች አይደለም።
- የኢስላም ሃይማኖት ተግባራዊነት በግላዊ ምልከታና አንድን ነገር መልካም አድርጎ በማየት ሳይሆን መልክተኛውን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመከተል ነው።
- ይህ ሐዲሥ የኢስላምን ምሉእነት የሚጠቁም ነው።
- ቢድዓ (መጤ) ማለት: በነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘመንና በሶሐቦች ዘመን ያልነበረ ሁሉም በሃይማኖት ውስጥ የተፈጠረ እምነታዊ ጉዳይ ወይም ንግግር ወይም ተግባር ነው።
- ይህ ሐዲሥ ከኢስላም መሰረቶች መካከል አንድ መሰረት የሆነና ለተግባራቱም እንደሚዛን የሆነ ሐዲሥ ነው። የትኛውም የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ስራ ባለቤቱ በስራው ምንዳ እንደማያገኝበት ሁሉ ልክ እንደዚሁ መልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይዘው የመጡትን ያልገጠመ የትኛውም ስራም በባለቤቱ ላይ ተመላሽ ይሆናል።
- የተከለከለው አዲስ ፈጠራ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ላይ ነው እንጂ አለማዊ ጉዳይ ላይ አይደለም።