- እነዚህ መጠበቂያ ዱዓዎች ከዱንያና ከመጨረሻው ዓለም ክፋቶች መጠበቅን ከሰበሰቡ አንገብጋቢና ጠቅላይ ከሆኑ ዱዓዎች መካከል ናቸው።
- የቀብር ቅጣት የተረጋገጠና እውነት መሆኑን እንረዳለን።
- የፈተናን አደገኝነት እና ከፈተና ለመዳን በአላህ መታገዝና ዱዓ ማድረግ እንደሚገባ እንረዳለን።
- የደጃል መውጣት የተረጋገጠ መሆኑንና ፈተናው ከባድ መሆኑን እንረዳለን።
- ከመጨረሻው ተሸሁድ በኋላ ይህን ዱዓ ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ከመልካም ስራ በኋላ ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።