- በሁሉም ሶላት ውስጥ የዚህ ተሸሁድ ስፍራው ከመጨረሻው ሱጁድ በኋላ በምንቀመጥበት ወቅት እና ባለ ሶስትና አራት ረከዓ ሶላት ከሆነ ደግሞ ከሁለተኛው ረከዓ በኋላም ነው።
- በተሸሁድ ወቅት "አትተሒያቱ" ግዴታ መሆኑን እንረዳለን። ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከተረጋገጡ የተሸሁድ ቃላቶች መካከል በማንኛውም ቢጠቀም ይበቃለታል።
- ሶላት ውስጥ በወንጀል እስካልሆነ ድረስ በማንኛውም ደስ ባለው ዱዓእ ማድረግ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- ዱዓ ላይ ከነፍስ መጀመር እንደሚወደድ እንረዳለን።