- ከተሸሁድ አባባች መካከል አንዱ አባባል መገለፁን እንረዳለን።
- የሶላት ድርጊቶችና ንግግሮች ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተረጋገጠ መሆኑ የግድ ነው። ለአንድም ሰው በሶላት ውስጥ በሱና ያልተረጋገጠን ቃል ወይም ድርጊት መፈልሰፍ እንደማይፈቀድ እንረዳለን።
- ኢማምን መቅደምም ሆነ ከርሱ መዘግየት እንደማይፈቀድ እንረዳለን። ለተከታይ የተደነገገው ኢማምን በድርጊቶች መከተሉ ነው።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዲኑን ለማድረስና ለኡመታቸው የዲን ህግጋትን ለማስተማር የሰጡት ትኩረት መወሳቱን እንረዳለን።
- ኢማም ለተከታይ መሪ ስለሆነ ተከታይ ከኢማሙ ጋር በሶላት ድርጊቶች ሊቀድመው፣ እኩል ሊሆንና ሊዘገይ አይፈቀድለትም። በተቃራኒ የመከተሉ ጅማሮ መሆን ያለበት ሊሰራው ወደ ፈለገው ድርጊት ኢማሙ መግባቱን እርግጠኛ ከሆነ በኋላ ነው። ሱናው በሶላት ድርጊቶች ኢማሙን መከተል ነው።
- በሶላት ውስጥ ሰልፎችን ማስተካከል መደንገጉን እንረዳለን።