/ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።...

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።...

ከሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል 'ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ' 'ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!' ይሉ ነበር።"
አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሁለቱ ሱጁዶች መካከል በሚቀመጡ ጊዜ "ረቢጝፊርሊ ረቢጝፊርሊ" "ጌታዬ ሆይ! ማረኝ! ጌታዬ ሆይ! ማረኝ!" ይሉ ነበር። ይደጋግሟትም ነበር። "ረቢጝፊርሊ" ማለት አንድ ባሪያ ከጌታው ወንጀሎቹን እንዲምረውና ነውሮቹን እንዲሸሽግለት መፈለጉ ነው።

Hadeeth benefits

  1. በግዴታም ሆነ ሱና ሶላት ውስጥ በሁለቱ ሱጁዶች መካከል ይህንን ዱዓ ማድረግ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  2. "ረቢጝፊርሊ" "ጌታዬ ሆይ! ማረኝ" የሚለውን ዚክር መደጋገም እንደሚወደድ እንረዳለን። ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ማለት ነው።