- ሶላተል ጀመዓን በመስጊድ ከመስገድ የመራቅ አደገኝነትን እንረዳለን።
- ሙናፊቆች በአምልኳቸው ይዩልኝና ይስሙልኝ በስተቀር ሌላ ምንም አያስቡም። ሰዎች በሚያያቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር ወደ ሶላት አይመጡም።
- ከጀመዓ ጋር ዒሻና ፈጅርን የመስገድ ምንዳ ትልቅነቱን እንረዳለን። እየዳኹ እንኳ ቢሆን ወደነሱ መምጣት የተገባ ነው።
- ዒሻና ፈጅር በመስገድ ላይ መጠባበቅ ከንፍቅና መንፃት መሆኑን ከነርሱ መቅረት ደግሞ የሙናፊቆች ባህሪ መሆኑን እንረዳለን።