- የዐስርን ሶላት በመጀመሪያ ወቅቱ በመጠባበቅ ላይና ወደዚህ ተግባር በመቻኮል ላይ መነሳሳቱ፤
- የዐስርን ሶላት የተወ ሰው ላይ ብርቱ ዛቻ መምጣቱንና ዐስርን ከወቅቱ ማሳለፍ ሌሎችን ሶላቶች ከወቅቱ ከማሳለፍ የበለጠ እጅግ ከባድ መሆኑን እንረዳለን። የዐስር ሶላት {በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡} [አልበቀራህ: 238] በሚለው የአላህ ንግግር ላይ ባለው ትእዛዝ ልዩ ሆና የተወሳች ምርጧ ሶላት ናትና።