- የፈጅርና የዐስር ሶላት ላይ መጠባበቅ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን። የፈጅር ሶላት ጣፋጭ እንቅልፍ የሚኖርበት ወቅት ሲሆን ዐስር ደግሞ ሰዎች በስራ የሚጠመዱበት ወቅት ነው። እነዚህን ሶላቶች ተጠባብቆ የሰገደ ሰው ሌሎቹንም ሶላቶች ተጠባብቆ መስገዱ አይቀርም።
- የፈጅርና የዐስር ሶላት በቀዝቃዛ ወቅት የተሰየሙት የፈጅር ሶላት የምሽት ቅዝቃዜ ያለባት ወቅት ስለሆነ ሲሆን የዐስር ሶላት ደግሞ የቀኑ ቅዝቃዜ ስላለባት ነው። በሙቀት ወቅት ብትሆንም እንኳ ሙቀቷ ከርሷ በፊት ካለው ሙቀት አንፃር ቀዝቀዝ ያለ ነው። ወይም በዚህ የተሰየመው በማቆረኘት መልኩ ነው። ልክ ለፀሀይና ለጨረቃ ሁለቱ ጨረቃዎች እንደሚባለው ማለት ነው።