- ከመፀዳጃ ስፍራ ሲወጣ "ጉፍራነክ" ማለት እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሁሉም ሁኔታቸው ጌታቸውን ምህረት እንደሚጠይቁ እንረዳለን።
- ከመፀዳጃ ቤት ሲወጣ ምህረትን የሚጠየቅበት ምክንያት አላህን ለብዙ ፀጋዎቹ ከማመስገን ስላጓደልን ሲሆን ከነዛም ፀጋዎቹ መካከል የሚያውከንን ነገር እንዲወጣ ማቅለሉ አንዱ ነው። በምፀዳዳበት ወቅት አንተን ከማውሳት ስለተጠመድኩ ምህረትህን እጠይቅሃለሁ ይባላልም ብለዋል።