- ነገር ማሳበቅ (ማዋሰድ) እና ከሽንት መጥራራትን መተው ከትላልቅ ወንጀሎች የሚመደብና ከቀብር ቅጣት ምክንያቶችም አንዱ ነው።
- ጥራት የተገባው አላህ እንደ ቀብር ቅጣት የመሰሉ አንዳንድ የሩቅ ምስጢሮችን ለርሳቸው መግለጡ የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የነቢይነት ምልክት ግልፅ ለማድረግ ነው።
- ቅጠልን ለሁለት ሰንጥቆ ቀብር ላይ ማድረግ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ብቻ የተለዩበት ስራ ነው። ምክንያቱም አላህ ለርሳቸው የቀብሩን ባለቤቶች ሁኔታ አሳውቋቸው ነውና ያደረጉት። የቀብርን ባለቤቶች ሁኔታ አንድም የሚያውቅ ስለሌለ ከርሳቸው ውጪ ያለን አካል በርሳቸው አንቀይስም (የርሳቸው ተመሳሳይ ብይን አንሰጠውም)።