- ነብዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አኼራ ላይ ሸፋዓ እንደሚያደርጉና ሸፋዓቸውም ተውሒድ ላላቸው ሰዎች መሆኑን ያፀድቃል፤
- የነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሸፋዓ ተውሒድ ላይ እያለ (በኃጢዓቱ ምክንያት) ጀሀነም የተፈረደበትን ወደ ጀሀነም እንዳይገባ፤ ከገባ ደግሞ እንዲወጣ የሚያደርጉት ምልጃ ነው፤
- ለአላህ ጥርት ተደርጋ የተባለች የተውሒድ ቃል ያላት ትሩፋትና የምታሳድረው ከፍተኛ ፋና፤
- የተውሒድ ቃል የሚረጋገጠው ትርጉሟን በማወቅና በምታስፈርደው ተግባራዊ በማድረግ ነው፤
- አቢ ሁረይራ ያላቸውን ደረጃና በዕውቀት ላይ ያላቸውን ጉጉት እንረዳለን።