- ከእንቅልፍ ተነስቶ እንኳ ባይሆን ዉዱእን ሲጀምር እጁን እቃ ውስጥ ከመክተቱ በፊት ሁለት እጆቹን መታጠቡ እንደሚወደድለት እንረዳለን። ከሌሊት እንቅልፍ ነቅቶ ከሆነ ግን እጆቹን ማጠቡ ግዴታ ነው።
- አንድ አስተማሪ ተማሪዎቹ ዕውቀቱን የሚገነዘቡበትንና የሚሰርፅበትን ቀላል መንገድ መጠቀም ይገባዋል። ከዚህም መካከል በተግባር ማስተማር ነው።
- አንድ ሰጋጅ ከዱንያ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ አዘናጊ ውልታዎችን ማስወገድ ይገባዋል። የተሟላ ሶላት ልብን ሶላቱ ውስጥ በመጣድ ነው የሚገኘው። ያለበለዚያ ከማሰብ ሙሉ ለሙሉ መፅዳት አስቸጋሪ ነው። እሱም ነፍሱን መታገልና ሀሳቡን ሶላቱ ላይ መገደብ ይገባዋል።
- ዉዱእ ላይ ቀኝን ማስቀደም እንደሚወደድ፤
- በመጉመጥመጥና አፍንጫ ውስጥ ውሀ አስገብቶ በማስወጣት መካከል ቅደም ተከተሉን መጠበቅ የተደነገገ መሆኑን ፤
- ፊትን፣ ሁለት እጅንና ሁለት እግርን ሶስት ሶስት ጊዜ መታጠብ እንደሚወደድ እንረዳለን። ግዴታው ግን አንድ ጊዜ ነው።
- ላሳለፍነው ወንጀል የአላህን ምህረት ለማግኘት ሁለት ነገሮች መሰባሰባቸውን ተከትሎ ነው የሚገኘው፤ እነሱም ዉዱእ እና ሐዲሡ ላይ በተጠቀሰው መልኩ ሁለት ረከዓ መስገድ ናቸው።
- ሁሉም የዉዱእ አካላቶች ክልል አላቸው። የፊት ክልል: በርዝመት ከተለመደው የራስ ፀጉር መብቀያ እስከ ፂም መውረጃና አገጭ ድረስ በጎን ደግሞ ከጆሮ እስከ ጆሮ ነው። የእጅ ክልል ደግሞ: ከጣቶች ጫፍ እስከ ክርን ነው። የጭንቅላት ክልሉ ደግሞ ከተለመደው ፀጉር መብቀያና የፊት ጎኖች እስከ ላይኛው ማጅራት ነው። ሁለት ጆሮዎችን ማበስ ጭንቅላትን ማበስ ውስጥ የሚካተት ነው። የእግር ክልሉ ደግሞ: ሙሉ ተረከዝን በእግሩና በባቱ መካከል ከሚለየው አጥንት ጋር ማጠብ ነው።